Friday, August 17, 2012

ደብረ ታቦር


ሠናይ ለነ ህልዎዝየ
በዚህ መሆን ለኛ መልካም ነው፡፡                       
       በጎፋ ቤዛ/ብዙኃን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ካቴድራል መዝገበ ምሕረት በህፃናት ክፍሉ የተዘጋጀ፡፡
      ይህንን ቃል የተናገረው ቅዱስ ጴጥሮስ ነው፡፡ ጴጥሮስ ማለት መሠረቱ የማይነቃነቅ አለት ማለት ነው፡፡ ማር 3፡6 የሐዋርት ሁሉ ተጠሪ እንዲሁም የሚስጢር ሐዋርያ ከሚባሉት አንዱ ነው ጴጥሮስ ዓሳ አስጋሪነት (አሳ አጥማጅነት)ከወንድሙ እንድሪያስ ጋር በስተርጅና የተጠራ ሐዋር ነው፡፡ ከጌታችን እግር ስር በመሆን ታዕምሩና ትምህረቱ ሁሉ ይከታተል የነበረ ሐዋሪያን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የኢያእሮስን ልጅ ሲያስነሳ አላዛርን ከሙታን ሲስነሳ በስሞን ቤት መዐድ ተቀምጦ የኦሪትን መስዋዕት ሽሮ የአዲስ ኪዳንን ሰተካ ጴጥሮስ ከጌታችን ጋር ነበረ፡፡ ከላ የተናገረውን ቃል ከሐዋርት መካከል ሦስቱ የምስጢር ሐዋር የሚባሉ ጴጥሮስ ያቆብ እና ዮሐንስ ይዞ ወደ ረዥም ተራራ አወጣቸው ከቤሔረ ሄዋን ነብዩ ኤሊያስን ከብሔረ ሙታን ደግሞ ነቢዩ ሙሴ እንዲሁም ካገባ ነቢዩ ሙሴን ከደናግል ነቢዩ ኤሊያስን አመጣ በፊታቸውም ተለወጠ ፊቱም እንደ ፀሐይ ልብሱም እንደብርሃን ነጭ ሆነ፡፡ ኤልያስና ሜሴን ከፈጣሪቸው ጋር ሲነጋገሩ ታየዋቸው ከነቢያት ሁለት ከሐዋርያት ደግሞ ሦስት በድምሩ አምስት አንድ ላይ ሆነው ታዩ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም ህንን ሲያይ እንዲህ አለ ‹‹ ሰና ለነ ህልዋዝየ›› በዚህ መኖር ለኛ መልካም ነው፡፡ እሱም ገና ህንን ሲናገር ብሩህ ደመና መጥቶ ጋረዳቸው በእነርሱም ደስ የሚለኝ ልጄ ይሄ ነው፡፡ እሱን ስሙት የሚል ቃል መጣ ደቀማዛሙርቱ ይህንን ሰምተው በግንባራቸው ወደቁ እጅግ ፈርተው ነበር፡፤ ጌታችንም ቀርቦ ዳሰሳቸው ተነሱ አትፍረም አላቸው፡፡አይናቸውንም አቅንተው አዩ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ በቀር ማንም አላገኙም በዚህም ነገር ጴጥሮስ ዮሐንስ ያዕቆብ ተደሰቱ፡፡ ከዚህ በኋላ የሚስደስት ነገር የለምና ሁል ጊዜ የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ጋር ሲኖር ይደሰታል፡፡ ከመከራና ከዳቢሎስ ፈተና ድል ያደርጋል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢሱስ ክርስቶስ ወደ ተራራ ሦስቱን ሠዋርያ እንዲሁም ሙሴንና ኤሊያስን ማምጣቱ ምስጢር አለው፡፡
ተራራ የቤተክርስቲያን ምሣሌ ነው፡፡

        ብሉይም አዲስም ይነገርባታ ይፀምባታል ሁለቱም አንድ ሆነው ይገለገሉበታል፡፡ጌታችንም ከብሉይ ኪዳን ሙሴና ኤልያስን ከአዲስ ኪዳን ሦስቱን ሀዋርያ ያመጣበት ምክንያት ሁለቱም ኪዳናት በደብረ ታቦር በቅዱስ ጋብቻ የጸኑ እና ድንግል እኩል በፈጣሪቸው ፊት መቆማቸውንም ለማሳየት በቤተክርስቲናችንም ደናግል መነኮሳትም ሕጋዊ ካህናትም አንድ ሆነው ያለ ልዩነት የሚያገለግሉባት ቅድስት ቤተክርስቲያን መሆኗን ለማጠየቅ ነው፡፤ ቅዱስ ጴጥሮስ በደብረ ታቦር ብርሃ መለኮቱን ሲይ በዚህ መኖር ለና መልካም ነው ብሎ ተናገረ፡፤ የሰው ልጅም በተቀደሰው ተራራ ቤተክርስቲን መገኘቱ መልካም ነው፡፡ መነሻውም መድረሻውም ቅድስት ቤተክርስቲያን መገነት ቤተክርስቲያን ናትና፡፤ የቤተክርስቲያን ድምፅ ለህወት ሥጋ እና ለሕወተ ነፍ
ሥ የሚበጅ ነው፡፤ በቤተክርስቲያን መገኘት በሰንበት ት/ቤት ዘወትር መማር እንዲሁም ከዓለም በመሸሽ ከእግዚአብሔር ጋር መኖር ለኛ መልካም ነው፡፤ ከዓለም በመውጣት በተራራ መኖር/በቤተክርስቲያን / መኖር መልካም ነውና፡፡
ተራራ የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ነው
        ተራራ ላይ መውጣት ብዙ ድካም ብዙ ጉልበት ማውጣት እንደሚጠይቅ ሁሉ ወደ መንግሥተ ሰማይ ለመግባት ብዙ ፈተና ብዙ መከራ አለበትና ወደተራራ ሲወጡ በቀስታና በእርጋታ በማስተዋል መውጣት አለብን ካለዚያ ግን ወድቆ መሰበር ወደ ገደል ገብቶ መሞት አለና ለዚህም ቅዱስ ጳውሎስ በዕብራዊያን መልዕክቱ ምዕራፍ 12፡2 ‹‹ከፊታችን ያለውን እሩጫ በትዕግስት እንሩጥ ›› በማለት እንደተናገረ፡፡ መንግሥተ ሰማያት ለመግባት ፣ ለመውረስ አንዱና ትልቁ መሳሪያ ትዕግስት ነው፡፡ እንዲሁም በማስተዋል በመራመድ እምነትን ጠንቅቆ በማወቅ ዕለት ዕለትም የእግዚአብሔርን ቃል በመማር ራስን መፈተሸ ይኖርብናል፡፡ ያለዚያ ግን በሐሰት ትምህርት በመውደቅ በመናፍቃን ትምህርት መሞት ስላለ መንግሥተ ሰማይ ለመግባት በማስተዋል በጥንቃቄ መጓዝ ይኖርብናል፡፡ በደብረ ታቦር የተደረጉት ሁሉ እያንዳንዱ ነገሮች ምስጢር አላቸው፡፡ በዓለሁንም ስናከብር ምስጢሩንም በተራራ ላይ የተገኙት ቅዱሳን ነቢያትና ሐዋርያት ሚስጥራዊ ምክንያት የተነገረው ትንቢታዊ ቃል በማስተዋል መሆን አለበት ከደብረ ታቦር ከተደረጉት ምስጢር መካከል የተወሰኑትን ቤተክርስቲን በትውፊት ተቀብላ ውሳኔ አድርጋ በዓሉን ታከብራለች፡፡ በትውፊት በዓሉም ቡሄ ተብሎ ይጠራል፡፡
        ቡሄ ማለት ብራ ብርሃን ደማቅ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮት የገለጠበት በዓል የሚዘከርበት ነው፡፤ በዓሉም ችቦ ስለሚበራ ብርሃነ መለኮቱ እናስብበታለን፡፡ እንዲሁም ድምፁን ስንሰማ የባሕሪ አባቱን የአብን ምስክርነት ቃል እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ያስታውሰናል፡፡
ችቦ ማብራት
        የጌታችንን ብርሃን የሚያመለክት ነው፡፤ በመሆኑም ለኩሰን በዓሉን እናከብራለን አንድም በደብረታቦር የነበሩ እረኞች የጌታችን ብርሃን በገለፀበት ጊዜ እረኞች በሜዳ ነበሩ፡፡ በጌታችን ብርሃን መምሸቱን ያልተረዲት እረኞች ቀርተው ነበረ እና ወላጆቻቸው ከመንደሩ እንጨት ሰብስበው /ችቦ/ለከሱ ልጆቻቸውን ፍለጋ መሄዳቸውን ታሪኩ ይዘክርበታል፡፡ በዓሉንም እናከብራለን፡፡
የችቦ መንደድ ሌለው ትርጉም አንድ ምመን መከራ አስተማሪ መሆኑን ያሳያል፡፡ በሃይማኖትም በዓርዓያም ምሳሌ ይሆናል፡፡
ሙልሙል ዳቦመጋገሩ
ልጆቻቸውን ፍለጋ የወጡ ወላጀች ሙልሙል ዳቦ ጋግረው ይዘው መጥተዋል፡፡ ይህን አናስታውስበታለን፡፡ ስጦታው ቤተሰባዊነት ምክርን ፍቅርን መተሳሰብን መግለፁ ነው፡፡ ወደቤታችን ቡሄ እሉ የሚመጡ ታዳጊዎች ዝማሬውን እንዳበቁ የሚሰጥ ሙልሙል ዳቦ አለ ለምሳሌ ሐዋርት የምስራች ሲነግሩ ወንጌል ሲሰብኩ በደጅ ይቆማሉ ቡሄ በሉ ታዳጊዎች የሚሉት በስጦታችንም ምሳሌያዊ መጽሐፍ ነው፡፡ ጌታችን ደቀመዛሙርቱን በአስተማራችሁበት በደረሳችሁበት ተመገቡ ብሎአቸዋል፡፡ ማቲ 10፡12 ህፃናቱም ሊዘም ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ አይደለም፡፤ ህፃናቱ የደቀ መዛሙርቱ ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ ሐዋርያት የምስራች ይዘው በመምጣታቸውምሳሌ ነው፡፡ ሐዋርያት በገቡበት ሀገር አስተምረው አጥምቀው የፀጋ ልጅነትን አሰጥተው እንደሚሄዱ ሁሉ ልጆችም ዘምረው፣አመስግነው፣መርቀው.ውለዱ፣ክበዱ፣በእምነት ፅኑ በማለትየመንግስተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ብለው ይመርቃሉ፡፤
        ዝማሬውም እንዲህ የሚል ነው፡፡
በአጠቃላይ ደብረታቦር ከሚቀርብባቸው ትርጓሜ ከትውልድ ወደ ትውልድ ከተላለፈ ቅዱስ ቱፊት ጋር ሃይማኖታዊ ሆኖ ሊቀጥል ይገባል፡፡ ይህንንም ማድረግ የሚቻለው ታዳጊዎችን እምነታቸውን ፊታቸውን ይኸው እንዲቆዩ በእምነትና በምግባር እንዲያድጉ አዘውትረን ውደ ቤተክርስቲያን ወደ ሰንበት ት/ቤት በመሄድ መማር ይኖርብናል፡፡ ቤተክርስቲያኗም የሚስጥር ስንዱ እመቤት ናት፡፡ የምታከናውነው ሁሉ ከበቂ መረጃ ጋር ተግባራዊ ታደርጋለች ወጣቱም ክፍል ይህን አውቆ ተረድቶ ለቀሪው ትውልድ ማስተላለፍ እንዲችል ከሰይጣን ፈተና ከክፋት ለመዳን ወደ ተራራ ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን መሸሸ የስፈልጋል፡፡ ቤተክርስቲያን በሰንበት ት/ቤት የሚማር ሁሉን ማየት የሚችል እና አስተዋይ ይሆናል፡፡ በስነ-ምግባርም የታነፀ ሀገሩን ወገኑን የሚጠቅም ሰው መሆን ይችላል፡፡
        ወደ ቅዱስ ተራራ /ቤተክርስቲያን/ ዕለት ዕለት እንወጣ ዘንድ እግዚአብሔር ርዳን!! የእመቤታችን ምልጃዋ ፀሎቷ ርዳን አሜን!!
በጎፋ ቤዛ/ብዙኃን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ካቴድራል መዝገበ ምሕረት በህፃናት ክፍሉ የተዘጋጀ፡፡

No comments:

Post a Comment