ሠናይ ለነ ህልዎዝየ
በዚህ መሆን ለኛ መልካም ነው፡፡
በጎፋ ቤዛ/ብዙኃን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ካቴድራል መዝገበ
ምሕረት በህፃናት ክፍሉ የተዘጋጀ፡፡
ይህንን ቃል የተናገረው ቅዱስ ጴጥሮስ ነው፡፡
ጴጥሮስ ማለት መሠረቱ የማይነቃነቅ አለት ማለት ነው፡፡ ማር 3፡6 የሐዋርት ሁሉ ተጠሪ እንዲሁም የሚስጢር ሐዋርያ ከሚባሉት አንዱ
ነው ጴጥሮስ ዓሳ አስጋሪነት (አሳ አጥማጅነት)ከወንድሙ እንድሪያስ ጋር በስተርጅና የተጠራ ሐዋር ነው፡፡ ከጌታችን እግር ስር በመሆን
ታዕምሩና ትምህረቱ ሁሉ ይከታተል የነበረ ሐዋሪያን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የኢያእሮስን ልጅ ሲያስነሳ አላዛርን ከሙታን ሲስነሳ በስሞን ቤት መዐድ ተቀምጦ የኦሪትን መስዋዕት ሽሮ የአዲስ
ኪዳንን ሰተካ ጴጥሮስ ከጌታችን ጋር ነበረ፡፡ ከላ የተናገረውን ቃል ከሐዋርት መካከል ሦስቱ የምስጢር ሐዋር የሚባሉ ጴጥሮስ ያቆብ
እና ዮሐንስ ይዞ ወደ ረዥም ተራራ አወጣቸው ከቤሔረ ሄዋን ነብዩ ኤሊያስን ከብሔረ ሙታን ደግሞ ነቢዩ ሙሴ እንዲሁም ካገባ ነቢዩ
ሙሴን ከደናግል ነቢዩ ኤሊያስን አመጣ በፊታቸውም ተለወጠ ፊቱም እንደ ፀሐይ ልብሱም እንደብርሃን ነጭ ሆነ፡፡ ኤልያስና ሜሴን ከፈጣሪቸው
ጋር ሲነጋገሩ ታየዋቸው ከነቢያት ሁለት ከሐዋርያት ደግሞ ሦስት በድምሩ አምስት አንድ ላይ ሆነው ታዩ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም ህንን
ሲያይ እንዲህ አለ ‹‹ ሰና ለነ ህልዋዝየ›› በዚህ መኖር ለኛ መልካም ነው፡፡ እሱም ገና ህንን ሲናገር ብሩህ ደመና
መጥቶ ጋረዳቸው በእነርሱም ደስ የሚለኝ ልጄ ይሄ ነው፡፡ እሱን ስሙት የሚል ቃል መጣ ደቀማዛሙርቱ ይህንን ሰምተው በግንባራቸው
ወደቁ እጅግ ፈርተው ነበር፡፤ ጌታችንም ቀርቦ ዳሰሳቸው ተነሱ አትፍረም አላቸው፡፡አይናቸውንም አቅንተው አዩ ከጌታችን ከኢየሱስ
ክርስቶስ ብቻ በቀር ማንም አላገኙም በዚህም ነገር ጴጥሮስ ዮሐንስ ያዕቆብ ተደሰቱ፡፡ ከዚህ በኋላ የሚስደስት ነገር
የለምና ሁል ጊዜ የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ጋር ሲኖር ይደሰታል፡፡ ከመከራና ከዳቢሎስ ፈተና ድል ያደርጋል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን
ኢሱስ ክርስቶስ ወደ ተራራ ሦስቱን ሠዋርያ እንዲሁም ሙሴንና ኤሊያስን ማምጣቱ ምስጢር አለው፡፡
ተራራ የቤተክርስቲያን ምሣሌ ነው፡፡