Tuesday, June 19, 2012

የመላዕክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል

ሚካኤል ማለት ‹እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው; ማለት ነው፡፡ ይህም የእግዚአብሔርን ገናንነትና እሱን የሚመስል አምላክ እንደሌለ የሚያመለክት ነው እንደ እግዚአብሔር ያለ ቅዱስ ንጹሕ ርህሩህ ኃይል ረቂቅ ማነው መልሱ የለም ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል የስሙ ዘርፍ ሆነው የሚጨመሩ መጠሪያዎች አሉት እነዚህም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠውን የባለሟልነት ክብር የሚገልጹ ናቸው፡፡ ይኸውም መልአከ ኃይል፣ መጋቤ ብሉይ፣ መልአከ ምክሩ…ናቸው፡፡ መልአከ ኃይል የተባለው እግዚአብሔር በሱ አማካይነት ታላላቅ ሥራዎችን በመሥራት ኃይሉን ስለገለጸ$ ዲያብሎስን ከነሠራዊቱ ስላሸነፈ ነው፡፡ መጋቤ ብሉይ የተባለበት ምክንያት በብሉይ ኪዳን ውስጥ ከእግዚአብሔር እየተላከ ብዙ ታላላቅ ሥራዎችን የሠራ በመሆኑ ነው፡፡


መልአከ ምክር ወይም የእግዚአብሔር የምክሩ አበጋዝ የተባለበት ምክንያት እግዚአብሔርን በምክሩ ይረዳዋል ለማለት ሳይሆን እግዚአብሔር የሚሠራውን ሥራ ለወዳጁ ለቅዱስ ሚካኤል ይገልጽለታል በሱም አማካኝነት ይሠራል ለማለት ነው፡፡

ቅዱስ ሚካኤል በመጽሐፍ ቅዱስ

Saturday, June 16, 2012

ነገረ ማርያም

«አልብኪ ነውር ወኢምንትኒ ላዕሌኪ፤» መኃ 4:7
                    
                                                                                ከኪዳነምህረት ድህረ ገፅ ላይ የተወሰደ
                                                                                         http://kidanemhret.org              
 
የትንቢተ ነቢያት ማረፊያ ፡-የስብከተ ሐዋርያት መነሻ.የሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ምሥጢር ነገረ ማርያም ነው፡፡ ያለ ነገረ ማርያም ነገረ ክርስቶስን መናገር አይቻልም፡፡ በክርስትና ሃይማኖት ታሪክ የተነሡ አያሌ መናፍቃን የመጀመሪያ ችግራቸው የነገረ ማርያምን አማናዊ ትምህርት መቀበል ነበር ፡፡ ያም ችግራቸው ክርስቶስን በትክክል እንዳያምኑት አድርጓቸዋል፡፡ በነገረ ማርያም ላይ የተጣራ ትምህርትና እምነት ቢኖራቸው ኖሮ ለኑፋቄ አይጋለጡም ነበር ፡፡ ንስጥሮስ፡- «አምላክ ወልደ አምላክ» ብሎ በክርስቶስ ለማመን የተሳነው « ወላዲተ አምላክ . ወላዲተ ቃል. እመ እግዚአብሔር » ብሎ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ለማመን በመቸገሩ ነበር፡፡

ነገረ ማርያምን ከነገረ ክርስቶስ መለየት አይቻልም ፡፡ የተዋሐደ ነው ፡፡ ስለ እመቤታችንየሚነገረው ክፉም ሆነ በጎ ክርስቶስን ይነካዋል፡፡ የእግዚአብሔርን የማዳን ሥራበምንናገርበት ጊዜ እመቤታችንን ወደ ጎን መተው አይቻልምና፡፡ ምክንያቱም ወልዳያስገኘች. አዝላ የተሰደደች. በማስተማር ጊዜው ከአገር አገር አብራው የተንከራተተችናትና ፡፡ በተሰቀለበት ዕለትም ከእግረ መስቀሉ አልተለየችም፡፡ በአጠቃላይ አነጋገርምክንያተ ድኂን አድርጓታል፡፡

Saturday, June 9, 2012

118ኛው የግብጽ ፓትርያርክ

 
ዳንኤል ክብረት እይታዎች የተወሰደ
117ኛው የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ታላቁ አባት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ 3 ሲያርፉ ዓለም በሙሉ ነበር ኀዘኑን የገለጠው፡፡ ክርስቲያኑና ሙስሊሙ፣ ቡድሂስቱና ሺንቶይስቱ፣ የሚያምነውና የማያምነው፣ የቻይናና የአሜሪካ ፖለቲከኞች፣ አንድ ሆነው በአቡነ ሺኖዳ ዕረፍት አዝነው ነበር፡፡
Coptic patriarchs
የእርሳቸውን ዕረፍት ተከትሎም የግብጽ ቤተ ክርሰቲያን እንዲህ ዓለምን በፍቅር አንድ አድርገው የሚገዙ ሌላ አባት ታገኝ ይሆን? የሚለው ጥያቄ ግብጻውያን ምእመናንን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ያሳሰበ ነበር፡፡ የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ለዚህ ጥያቄ መልስ ለመስጠት ዝግጅቷን ጀምአመራረጥ ራለች፡፡ በቤተ ክርስቲያኒቱ የአዲስ ፓትርያርክ ሥርዓት እጅግ የሚያስደስት፣ ለክርክርና ለሐሜት በር የሚዘጋ፣ አባቶችንና ምእመ ናንን የሚያሳትፍ፤ መንፈሳዊነቱንም የተሞላ ነው፡፡